Saturday, 31 May 2014

እጅህን እንዳትሰጥ!!


እናት 
ናልኝ እስክ ባባዬ፥ ጣለዉ እሱን ዱላ
ብትማር ይሻልሃል፥ እንዳትቀር ወደኋላ
ደብተርህን ይዘህ፥ ዝለቅ ከተማሪ ቤት
እስከመቼ ድረስ፥ ይብቃ እረኝነት

ልጅ
እኔ አልሄድም ማሚ፥ ባፊንጫዬ ይዉጣ
ትምህርት ቤት መሄድ፥ ምን ለዉጥ ልያመጣ
በጥይት መደብደብ፥ ሆኖ የኛ ዕጣ
እምቢ አልሄድም ማሚኮ ፥ ባፊንጫዬ ይዉጣ

እናት
ሳፉ ጎፍታ ዱጋ…
ሰምተህልኛላ፥ የሰሞኑን እሮሮ
ካዋቂዎች አልፎ፥ ዘልቋል ካንተም ጆሮ
ቢሆንም አብዲኮ ፥ ተስፋ አትቁረጥ
መፍትሄዉም መማር ነዉ፥ እጅህን እንዳትሰጥ!!

No comments:

Post a Comment